የቅድስት ማሪያም ዩኒቨርስቲ 17ኛውን የዘርፈ ብዙ ጥናት ጉባኤ እያካሄደ ነዉ

Date:

የቅድስት ማሪያም ዩኒቨርስቲ 17ኛውን የዘርፈ ብዙ ጥናት ጉባኤ በበርካታ ወቅታዊ ችግሮች ላይ በማተኮር በዛሬው ዕለት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የዩኒቨርስቲ መስራችና ፕሬዚዳንት ወንድወሰን ታምራት (ዶ/ር)፤ በጉባኤው የቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ ዲጂታላይዜሽን፣ የዋጋ ግሽበት፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፋይናንስ ስርአቶችን የሚደግፉ የህግ ማዕቀፎችን ጨምሮ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚያጠቃልል እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ጉባኤው ተመራማሪዎችን፣ ባለሙያዎችንና ባለድርሻ አካላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአካዳሚክ ልውውጥና የሂሳዊ አስተያየቶች የሚቀርቡበት መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ጉባዔው የትምህርትና ማህበራዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ አቀራረብን በመከተል ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ምሁራን ለችግሮች የመፍትሔ ሀሳብ የሚያበረክቱበት ስለመሆኑ ፕረዚዳንቱ ተናግረዋል።

የጉባኤውን ዘርፍ ብዘሃነት ለማመልከትም ከቅድስት ማሪያም ከዩኒቨርስቲ በተጨማሪ ከአርባምንጭ፣ ወራቤ፣ ባህር ዳር፣ ወልድያ እና መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ተመራማሪዎች ፅሁፋቸውን እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል።

ይህ ጥምረትም በዘርፎች መካከል ትብብር በመፍጠር ተፅዕኖ ፈጣሪ የጥናትና ምርምር ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ለፖሊስ አውጪዎች ግበዓት ሊሆኑ የሚችሉ እሳቤዎች በሰፊው የሚንፀባረቅበት እንደሆነ ወንድወሰን(ዶ/ር) የገለፁ ሲሆን፤ በጉባኤም 12 ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል።

ጋዜጣ_ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...