በማይናማር በአጋቾች እጅ ከሚገኙ  ኢትዮጵያውያን አንድ ሰው ራሱን አጠፋ

Date:


‎በማይናማር በ3 ካምፕ ውስጥ 42 ኢትዮጵያውያን ታግተው የአካል ጉዳት እየደረሰባቸው እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን የታጋች ወላጆች አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ በፊት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ አገር የመለሳቸው መኖራቸውን ያስታወሱት የወላጅ ኮሚቴ አባላት፤ አሁን ያሉት ግን ምንም አይነት ፕሮሰስ እንዳልተጀመረላቸዉ ገልፀዋል።

14 ልጆች በቅርብ ይወጣሉ መባሉን አንስተው፤ ቦታዉ ድረስ ሲሄዱ ግን ከፖሊስ ጋር ትብብር ስለሚያደርጉ እና ቀድሞ መረጃ ስለሚደርሳቸው ልጆቹን እንደሚደብቋቸዉ ተናግረዋል።

ከ42ቱ ታጋቾች መካከል 7ቱ ሴቶች መሆናቸውንም ሰምተናል።

የሚደርስባቸው ስቃይ እና ድብደባ ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት የወላጅ ኮሚቴ አባላት፤ ምግብ እንደማያገኙ እና ለሞት እና ለአካል ጉዳት እየተዳረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

‎ከዚህ በፊት ኮሚቴው በተደጋጋሚ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ጥረት በመጠለያ ካምፕ የነበሩ ከ7መቶ በላይ ዜጎች ከማይናማር ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እንደተቻለ ይታወሳል።

አሁን ላይ ቀሪዎቹ ልጆቻችን ወደ ሀገር እንዲመለሱ ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም ብለዋል፡፡

ላሚን ያማል በባርሴሎና የ10 ቁጥር  ማሊያን ተረክቧል

ተጨዋቹ የማሊያ ቁጥሩን  እንደሚለብስ ለማሳወቅ 18 አመት እስኪሞላው ድረስ  የተጠበቀ ሲሆን መጪዎቹ ጊዜያት ለበረከት እና እርግማን ከመዘጋጀት በላይ እንደሆነ ተግልጿል ።

በቅርቡ 18 አመቱን  ያከበረው ያማል ላለፉት 3 አመታት ሲለብሰው ከነበረው አንሱ ፋቲ ወደ ሞናኮ ማቅናቱን ተከትሎ የክለቡን ድንቅ ቁጥር  ተረክቧል ።

ባሳለፍነው አመት ከባርሴሎና ጋር የላሊጋ ፣ የኮፓ ዴላሬይ  እና የሱፐር ካፕ ዋንጫን ማሳካት የቻለው ተጨዋቹ በርካታ ጥቅም የሚስገኝለትን አዲስ  ኮንትራትም ተፈራርሟል ።

ውሳኔው በክለቡ እና በተጨዋቹ መካከል በስምምነት የተደረገ ሲሆን በሚቀጥሉት ጊዜያትም የማሊያው ሽያጭ ላይ የገንዘብ ጭማሪ እንደሚኖረውም  ተግልፅዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...