የቡሄ በዓልን ወደ ዓለማቀፍ መድረክ ማምጣት ያስፈልጋል

Date:

‎የቡሄ በዓልን ወደ ዓለማቀፍ መድረክ በማምጣትና በማስተዋወቅ ትልቅ የቱሪዝም መስህብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሐዱ ያነጋገራቸው ምሁራን ገልጸዋል።

‎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በመላው ሀገሪቱ በድምቀት የሚከበረው የቡሄ ወይም የደብረ ታቦር በዓል በነገው ዕለት ነሐሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ታስቦ ይውላል።

‎”የደብረ ታቦርን በዓል በደብረ ታቦር ከተማ” በሚል በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ በደብረ ታቦር ከተማ የሚከበር ሲሆን፤ በዚህም መሠረት “እንደቡሄ እና መሠል በዓላት ለቱሪዝም ዘርፉ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ እንዲሁም ቀጣይነት እንዲኖራቸው ከማን ምን ይጠበቃል?” ሲል አሐዱ ምሁራንን ጠይቋል።

‎በዚህም የአሐዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪ ጥበቡ በለጠ፤ “ኢትዮጵያ የበርካታ ታሪክ ባለቤት ከመሆኗም ባሻገር በብዙ ባህሎች የበለፀገች ሀገር ብትሆንም ያላትን እምቅ አቅም ለአለም ከማስተዋወቅ አንፃር ክፍተቶች ይታያሉ” ሲል ተናግሯል።

‎ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ያስመዘገበቻቸው እንደ ጥምቀት፣ መስቀል ደመራ እና መሰል በዓላት ቢኖሩም ሌሎች በቅርስነት ሊመዘገቡ የሚገቡ በዓላት መኖራቸውን ገልጿል፡፡

የቡሄ በዓልም ከሃይማኖታዊ ይዘቱ በተጨማሪ ልጆችና ወጣቶች በየሰፈሩ እየዞሩ የሚጨፍሩት ሲሆን፤ “ሀገራዊ አንድምታው ከፍ ያለ በመሆኑ ባህላዊ ትውፊቱ ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል” ብሏል።

‎ሌላኛው የወይንዬ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማህበር ሰብሳቢ መምህር ደረጀ ዘወይንዬ በበኩላቸው፤ “ደብረ ታቦር በዓልም ባህልም ነው” ያሉ ሲሆን፤ “በዓልነቱ ኢየሱስ  ክርስቶስ ብርሀነ መለኮቱን በታቦር ተራራ የገለጠበት ስለሆነ በዓል ሆኖ ይከበራል፤ በተጨማሪም ባህልነቱ ደግሞ የተለያዩ ባህላዊ ትውፊት የሆኑ ሥነ ስርዓቶች ይከናውኑበታል” በማለት ገልጸዋል።

“በዓሉ ‎የቱሪስት መስህብ ሆኖ እንዲቀጥል መስራት ከሁሉም የሚጠበቅ ሥራ ቢሆንም፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ግን ከፍተኛ ሚና መስራት ይጠበቅባታል” ሲሉም መምህር ደረጀ ለአሐዱ ተናግረዋል።

‎ከዚህ ባሻገርም የቡሄ በዓልን እንደ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን አይነት በመንግሥት ደረጃ ያሉ ተቋማት የቱሪዝም መስህብ እንዲሆንና ለሀገር አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችል ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ምሁራኑ ጠቁመዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...