የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ለቅዳሜ ገበያ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ሥርዓት ጥበቃ የሚደረግላቸው መብቶች የቅጅና ተዛማጅ መብቶች፣ ፓተንቶች (የግልጋሎት ሞዴሎችን ጨምሮ)፣ ኢንዱስትሪያዊ ንድፎች እና የንግድ ምልክቶች ናቸው፡፡
ባለስልጣኑ በተጠናቀቀው በጀት አመት በንግድ ምልክት፣ በፓተንት፣ የቅጅና ተዛማጅ መብቶችን ጨምሮ 4 ሺህ 959 ፍቃዶችን ሰጥቷል።
ተቋሙ ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጸው ፍቃድ ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል በንግድ ምልክት 3 ሺህ 386 ፍቃዶች ይገኝበታል።
ተቋሙበ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች 1 ሺ 220 ፍቃዶች እንዲሁም በአስገቢ ፓተንት ደግሞ 13 ፍቃድ ሊሰጥ ችሏል።
ከዚህም በተጨማሪ 57 በፓተንት ፍቃድ 175 በአገልግሎት ሞዴል እንዲሁም 108 በኢንዱስትሪያል ዲዛይን ፍቃድ መስጠቱን አስታውቋል።
