የባንኮች ቀን በኢትዮጵያ

Date:

የባንኮች  ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሊከበር ነው።

የባንኮች ቀን በጎዳና ላይ ሩጫ እና በኤግዚብሽን እንደሚከበር ተገልጿል።

አመቱን ሙሉ በትጋት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ሰራተኞቻቸዉን ቲሸርት ገዝተዉ የሚሳትፉበት ራሳቸዉን ከሌሎች የባንኩ ማህረሰብ ጋር የሚያስተዋዉቁበት አልፎም በሰራተኞቻቸዉ አማካኝነት ራሳቸዉን የሚያስተዋዉቁበት ፕሮግራም ነዉ ተብሏል።

ይህ አመታዊ ፕሮግራም ህዳር 21/2017 ዓ.ም የሚደረግ ይሆናል።

በዚህም በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የባንኩ ማህበረሰቦች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለተኛው ህዳር 25/2017 ዓ.ም የሚደረገው ኢግዚቢሽ ሲሆን ይህም ፕሮግራም ባንኮቹ ለተሳትፎ በተዘጋጀላቸዉ ድንኳኖች አገልግሎታቸዉን ያስተዋውቃሉ በዚህ ፕሮግራም ላይ ሁሉም ባንኮች በንቃት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የባንኮች ቀን የሚከበረዉ እ.ኤ.አ አቆጣጠር ዲሴምበር 4 ቀን ሲሆን የሚከበርበትም ዋናምክንያት ለህዝቡ ፋይናስ ደህንነት ባንክ መረጃን በመስጠት ለሚጫወተዉ የላቀ ሚና እዉቅናን ለመስጥ ነዉ፡፡

የፕሮግራሙ አዘጋጅ ማርዳ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ኤቨንትስ ካምፓኒ ሲሆን ከተቋቋመ ዘጠኝ ዓመት ያስቆጠረ የተለያዩ ፊልሞችን በመስራት እንዲሁም ኤቨንቶችን በማዘጋጀት በመዝናኛዉ ኢንዱስትሪ የራሱን አሻራ በማሳረፍ ላይ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...