የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ እና ሴራሊዮን ጋር ለሚያከናውናቸው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ 7ኛ እና 8ኛ ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።
በግብ ጠባቂነት – አቡበከር ኑራ፣ ቢኒያም ገነቱ እና ፍሬው ጌታሁን ተመርጠዋል።
በተከላካይ መስመር – አስራት ቱንጆ፣ ያሬድ ካሳዬ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ሱለይማን ሃሚድ፣ አህመድ ረሺድ፣ ራምኬል ጀመስ፣ ንጋቱ ገብረስላሴ፣ ያሬድ ባየህ እና ምኞት ደበበ ተካተዋል።
በአማካኝ ስፍራ – ሃብታሙ ካሳዬ፣በረከት ወልዴ፣ሃይደር ሸረፋ፣አብዱልከሪም ወርቁ፣ቢኒያም በላይ፣ከነአን ማርክነህ እና ወገኔ ገዛሃኝ ይገኙበታል።
በፊት መስመር ላይ – ቸርነት ጉግሳ፣ በረከት ደስታ፣ ኪቲካ ጅማ፣ ዳዋ ሁቴሳ፣ አህመድ ሁሴን፣ መሃመድ አበራ እና ቢኒያም አየነ በአሰልጣኙ ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች ናቸው።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች እስከ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ በጁፒተር ሆቴል እንዲሰባሰቡ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ወደ አዳማ በማምራት ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
