የተመድ ዋና ጸሃፊ እስራኤልን እና ሩሲያን አስጠነቀቁ

Date:


የእስራኤል እና የሩሲያ ወታደራዊና የጸጥታ ሃይሎች በጦርነት ቀጠናዎች ውስጥ በወሲባዊ ጥቃት ወንጀል ከተጠረጠሩ አካላት ዝርዝር ውስጥ ሊካተቱ እንደሚችሉ የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ጉተሬዝ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ከግጭት ጋር በተያያዙ በጾታዊ ጥቃቶች ዙርያ ዓመታዊ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ እስራኤል እና ሩሲያ በሚቀጥለው ዓመት “በአስገድዶ መድፈር ወይም በሌሎች የፆታዊ ጥቃት ዓይነቶች ተጠያቂ ናቸው ተብለው ከሚዘረዘሩ ወገኖች መካከል” ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ዋና ጸሃፊው እስራኤል በሚቀጥለው ዓመት “በአስገድዶ መድፈር ወይም በሌሎች የጾታዊ ጥቃቶች ተጠያቂ” ተብላ ልትዘረዝር እንደምትችል ጠቁመው፣ “በበካርታ እስር ቤቶች፣ ማቆያ ማዕከላትና ወታደራዊ ካምፖች ውስጥ የእስራኤል ጦርና የጸጥታ ኃይሎች በፍልስጤማውያን ላይ ስለሚፈጸሙ ጥሰቶች ከሚገኙ ተዓማኒ መረጃዎች” ጋር በተያያዘ “እጅግ አሳሳቢ ስጋት” እንዳላቸው ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ዋና ጸሃፊው በሪፖርታቸው ሩሲያ በዩክሬን እስረኞች የተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶችን ፈጽማለች ብለዋል። ይህንንም ያደረገችው እስረኞችን ለማዋረድና መረጃ ለማግኘት እንደሆነም ጠቁመዋል።

በጦርነት ቀጠናዎች ውስጥ ሴቶች ላይ የሚፈጸም የጾታ ጥቃት እጅግ እየተበራከተ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቀማሉ።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው

NBCEthiopia

ሆኖ_መ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...