የተረጋጋ ሀገር እንዲኖር በትምህርት ዘርፉ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል መስጠት ያስፈልጋል

Date:

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዳሰነች ወረዳ የተገነባውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመረቁበት ወቅት በትምህርት አቅርቦት ረገድ በሁሉም አካባቢ ምንም ልዩነት ሊፈጠር አይገባም ብለዋል።

ይህንንም ለማረጋገጥም በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ የሪፎርም ተግባራት ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኝም አብራርተዋል ። በተለይም ምቹ የመማሪያ ከባቢን በሁሉም አካባቢ ለመፍጠር “በትምህርት ለትውልድ” የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውንና የነባር ትምህርት ቤቶች ጥገና መደረጉን አንስተዋል።

አክለውም የትምህርት ስራ የሚለወጠው ከታች ጀምሮ ሲሰራ መሆኑን በማመን በከተማና በባለሀብቶች ብቻ ታጥሮ የቆየውን የቅድመ አንደኛ ትምህርት በመቀየር በሁሉም አካባቢ ያለ ልዩነት ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን ጠቅሰዋል። በዚህም ባለፉት ዓመታት ከ34 ሺ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በከተማና በገጠር ተገንብተው የአምስተና ስድስት ዓመት ህፃናት እየተማሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

ትምህርት ለሁሉ ነገር ወሳኝ በመሆኑ ልጆቻችንን በአግባቡ በማስተማር የአለምን ፈተና መቋቋም የሚችሉ ጠንካራ ሀገር ተረካቢዎችን ለመፍጠር መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል። አክለውም የትምህርት ሥራ ከፖለቲካ መላቀቅ አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ሁሉም ነገር ፖለቲካ መሆኑ ቀርቶ ትምህርት የሁላችን እንዲሆን በማድረግ ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት በማቅረብ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል በመስጠት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ብቻ ከ12ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ

በሱዳን የሚገኘው የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው መረጃ...

ትራምፕ አሜሪካ እና ኢራን “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ሊወያዩ እንደሚችሉ ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት...

የኢራን ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ የዓለም ምጣኔ ኃብት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አይኤምኤፍ አስጠነቀቀ

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው የኢራን...

የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የ፵ ቀን መታሰቢያ ጥሪ

​"የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው!" (ምሳሌ ፲፥፯)​በሕይወትና በቃል ትምህርታቸው ብዙዎችን...