የተሰረዙ የሲቪል ማህበራት ዳግም ወደ ሥራ መመለስ አይችሉም

Date:

የሥራ ሪፖርት ባለማቅረባቸው ምክንያት የተሰረዙ የሲቪል ማህበራት ዳግም ወደ ሥራ መመለስ እንደማይችሉ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ ማህበራቱ ወደ ሥራ መመለስ እና መስራት ከፈለጉ እንደገና ፈቃድ ማውጣት እና ሥም መቀየር እንደሚገባቸው ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን ተመዝግበው በሥራ ላይ ያሉት የሲቪል ማህበራት የትኞቹ ናቸው? የሚለውን ጉዳይ ለማጣራት በተሰራ ሥራ፤ ከ1 ሺሕ 700 በላይ የሲቪል ማህበራት ከሥራ ውጭ መሆናቸው መገለጹ የሚታወስ ነው።

እነዚህ ተቋማት 5 ዓመት እና ከዛ በላይ ተጠብቀው በመቅረታቸው እና ሲጣራ ከሥራ መውጣታቸው በመረጋገጡ መሰረዛቸውም ነው የተገለጸው።

አሐዱም “የሥራ ሪፖርት ባለማቅረባቸውና በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም የጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸው ባለማስተካከላቸው የተሰረዙ ማህበራት ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው? ዳግም ወደ ሥራ የሚመለሱበትስ አግባብስ ይኖር ይሆን?” ሲል የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴንን ጠይቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በምላሽቸው “ማህበራቱ በተለይም በክልሎች ተዘዋውረው የተለያዩ ሥራዎችን የሚሰሩትን ለመደገፍ እና እንዳይዘጉ ለማድረግ ቢያንስ የሥራ ሪፖርት ማቅረብ ባይችሉ ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ በሚል ውሳኔው ከተወሰነ በኋላ የሁለት ወር ጊዜ ቢሰጥም መምጣት አልቻሉም” ብለዋል፡፡

“በተቋሙ በኩል የሚገመቱ ጉዳዮች አሉ” ያሉት ኃላፊው፤ “እነሱም በሥራ ብዛት እና በጊዜ እጥረት ፈቃዱን ብቻ ይዘው የተቀመጡ እና ሄደን ዳግም ምዝገባ ብናደርግም ካልሰራንበት ጥቅም አይኖረውም የሚል ሁኔታ እንደሚኖር ተገምቷል” ነው ያሉት፡፡

የሲቪል ማህበረስብ ባለስልጣንም ይህን ግምት ውስጥ አስገብቶ ሰፊ የዳግም ምዝገባ ጊዜ እንደሰጠ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን በዚህ ጊዜ መምጣት እና ዳግም ምዝገባ ማድረግ የቻሉት ከ70 የማይበልጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ብቻ እንደሆኑም አንስተዋል።

“ተቋማቱ መጨመራቸው የሚፈለግ ነው” ያሉት አቶ አህመድ፤ “ለሱም በፊት ፈቃድ አውጥተው የተሰረዙ ተቋማት አዲስ ፈቃድ ማውጣት እና ሥም ቀይረው የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ አድርገው ወደ ሥራ መመለስ ይችላሉ” ብለዋል፡፡ 

ወደ ሥራ እንዲመለሱ ለማድረግ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ በሁሉም የግንኙነት አማራጮች መልዕክት እንደተላከ እና ምላሽ እንዳልሰጡም ተነግሯል።

ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
ዋትስአፕ፦ whatsapp.com/channel/0029VajDfVZI1rcb05C5B22b
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...