የተፈጥሮ ጋዝ የሚጠቀሙ ከባድ መኪኖች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ አገር እንዲገቡ ተፈቀደ

Date:

በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ማናቸውም ዓይነት የደረቅ እና የፈሳሽ ጭነት ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከዛሬ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅዷል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ይህን ያሳወቀዉ በቅርቡ በካሉብ አካባቢ የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ኢንዱስትሪ ተመርቆ የተፈጥሮ ጋዝ የማምረት ሥራ በይፋ ከተጀመረ በኋላ ነው።

ሚኒስትሩ እንዳብራራዉ ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያላት ቢሆንም ለዘመናት ተጠቃሚ ሳትሆን ቆይታለች።

በመሆኑም አዲሱ የጋዝ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲቀርብ በማድረግ፣ ቤንዚንና ናፍታ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን በተፈጥሮ ጋዝ በሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች መተካት ለአገር ወሳኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህ የጉምሩክ ቀረጥ ነፃ የማድረግ ማበረታቻ ውሳኔ የተገለፀው፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከሦስት ቀናት በፊት ባወጣው ማስታወቂያ ውስጥ በተጠቀሰው እገዳ ላይ ማብራሪያና ማበረታቻ ለመስጠት እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

ሚኒስትሩ አስመጪዎች እንዲያውቁት ባወጣው ማስታወቂያ በቀጣይ በተፈጥሮ ጋዝ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ እንደሚፈቀድ አስታውቋል።

ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በኋላ የሚደረጉ ከባድ መኪና ግዥዎች የማስገቢያ ፈቃድ እንደማይሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...