የቻይና ኩባንያ በኢትዮጵያ የአየር ታክሲና ሰው አልባ ተሽከርካሪዎችን ሊያመርት ነው

Date:

የቻይናው ሻንሀይ ላውንች ዲዛይን አውቶሞቲቭ ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የአየር ታክሲና ሰው አልባ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።

ይህንንም ፍላጎት ይፋ ያደረገው የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ው ሻውሀን ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ መንግስት አረንጓዴ ትራንስፖርትን ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው ጠንካራ የመንግስት ድጋፍ እና የታክስ ማበረታቻዎች ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች መሆናቸውን አስረድተዋል።

የሻንሀይ ላውንች ዲዛይን አውቶሞቲቭ ስራ አስኪያጅ እንዳሉት ኩባንያቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ መሰማራት እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

ኩባንያው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የአየር ታክሲና ሰው አልባ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ አውቶሞቢሎችን፣ አውቶብሶችንና የጭነት ተሽከርካሪዎችን እንደሚያመርትም አብራርተዋል።

ቅዳሜገበያ

Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...