የቀድሞው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ በ84 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ ከአውሮፓውያኑ 2001 እስከ 2009 የቀድሞ ሪፐብሊካን መሪ ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ምክትል በመሆን አገልግለዋል፡፡
ህልፈታቸውን ተከትሎ የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ፤ የቼኒ ህልፈት ለሀገር ትልቅ ኪሳራ፤ ለወዳጆቹ ደግሞ መሪር ሀዘን ነው ብለዋል፡፡
ቼኒ ሀገራቸውን የሚወዱ፣ለህዝብ የቆሙ፣ታታሪና እና የቅን ልብ ባለቤትም ነበሩ ሲሉ ቡሽ ገልፀዋቸዋል፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንቱ ህይወታቸው ያለፈው ባደረባቸው ከልብ እና ደም ቧንቧ ህመም ጋር በተያያዘ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል፡፡
ዲክ ቼኒ ከ1970 ማለትም ከፕሬዝዳንት ጄራልድ ፎርድ አመራር አንስቶ በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች በአሜሪካ ፖለቲካ ሀውስ ውስጥ ማገልገላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
