የአሜሪካ ኤምባሲ አቶ ማሞ ምህረቱን በይፋ አመሰገነ

Date:

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ ከሰሞኑ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው የለቀቁትን የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በይፋ አመሰገነ፡፡

ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት፤ አቶ ማሞ ለሰጡት አገልግሎትና ለራዕያቸው  ምስጋና አቅርቧል፡፡

“የአቶ ማሞ ድፍረት የተመላበት አመራር፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚና ህዝቧን ወደ ኋላ ይጎትቱ የነበሩ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን ለማረም ረድቷል” ብሏል፤ ኤምባሲው።

ኢትዮጵያ እሳቸው መንገድ የጠረጉለትን የኢኮኖሚ ማሻሻያ  እንድትቀጥልም  አሳስቧል።

ኤምባሲው አክሎም፤ “በተለይ ከባድ ተግዳሮቶች  ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ለውጥ በጭራሽ ቀላል አይደለም” ሲልም ለሪፎርሙ ዕውቅና በመስጠት የቀድሞውን የብሔራዊ ባንክ ገዢ አመስግኗል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...