ሲፒጄ የሸገር ጋዜጠኞች ከእስር እንዲፈቱ ጠየቀ

Date:

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ)፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ጸጋውን “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን፣ ጣቢያው በጤና ባለሙያዎች ዙሪያ የሠራው ዘገባ “ግጭት ቀስቃሽ” እና “አድሏዊ” ነው በማለት ጣቢያው ዘገባውን እንዲያነሳ በደብዳቤ ማዘዙን ሲፒጄ ጠቁሟል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ወደ ጣቢያው በመግባት የዜና ክፍል ሃላፊውን እሸቴ አሠፋን ጭምር ካሠረ በኋላ የዕለቱ’ለት እንደለቀቀው መስማቱንም ተቋሙ ጠቅሷል።

ሁለቱ ጋዜጠኞች ጳጉሜ 3 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ የተባሉ ሲሆን፤ ሲፒጄ “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” ከእስር እንዲፈቱ መንግሥትን ጠይቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...