የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፥ አቶ ታዬ ደንደዓ ላይ ወስኖት የነበረውን የ7 ዓመት ከ2 ወር እስራት ወደ 4 ዓመት ዝቅ ማድረጉን የፍርደኛው ገልጸዋል።
ጠበቃቸው አበራ ንጉስ መጋቢት 10 ችሎት ውሎ እንደነበር ገልጸው፣ ” ሁለት፣ ሦስት በቀዳሚነት ያስቀመጥናቸው የይግባኝ ቅሬታ ሳይቀበለን አልፎ ቅጣቱ የተጋነነ ነበር ብሎ በአራት አመት እስራት እንዲፈረድ አድርጎ ቀንሶታል፤ ከ7 አመት ከ2 ወር ወደ 4 አመት ” ብለዋል።
ይሁን እንጂ ውሳኔውን ” እኛ አሁንም አልተቀበልነውም ምክንያቱም እነዛ በቅደም ተከተል ያስቀመጥናቸው ወሳኝ የህግ መከራከሪያዎች በአግባቡ አልተመረመሩም ” ብለው ” ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቀብሎ ያጸናበት መንገድ መሰረታዊ ስህተት ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
” ኢ-ህጋዊ የሆነ ትንተና እና የህግ ግንዛቤ ታሳቢ አድርጎ የተወሰነ ስለሆነ ቀጣይ ወደ ሰበር ይግባኝ የምንቀጥል ይሆናል ” ብለው፣ ለዚህ ህጉን ተንተርሰው ዝርዝር ምክንያት አስቀምጠዋል።
” በአቶ ታዬ እና ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊቶች ተፈጽመዋል ተብሎ አንድ ክላሽ እና 60 ቀልሃ ይዘው የተገኙ ሰዎች ከ7 ወር በላይ ተቀጥተው አያውቁም ” ሲሉ ጠቅሰዋል።
ጠበቃ አበራ ንጉስ ስለይግባኝ ሂደቱ ምን አሉ ?
” አቶ ታዬ የጸና ፍቃድ ሳይኖረው ህገወጥ የጦር መሳሪያ መያዝ ጥፋተኛ ተብለው በከፍተኛ ፍርድ ቤት የ7 አመት ከ2 ወር ቅጣት ተላልፎባቸው፤ ለዚህም ይግባኝ ተጠይቆ ነበር።
ከመጀመሪያው የወንጀል ድርጊት የሚያቋቁም ድርጊት አልፈጸሙም። ስለዚህ አቃቤ ህግ ያቀረበው የወንጀል ክስ ስህተት ነው ወይም ሳይፈጸም ነው የቀረበባቸው የሚል ነበር።
ሁለተኛ ደግሞ መከላከያ ምስክሮቻችንን ዘርዝረን ካቀረብንባቸው መከላከያ ምስክሮች ወሳኞቹ 3 መከላከያ ምስክሮች በተደጋጋሚ ሳይሰሙ ታልፈው የተሰጠ የጥፋተኝነት ፍርድ ነው። ያም መሰረታዊ የሆነ ህገመንግስታዊ መብትን የተላለፈ ሂደት ነው።
ሦስተኛ፣ አቶ ታየ ካቀረቧቸው አምስት ምስክሮች ሁለቱ ሲሰሙ እንኳን አቶ ታዬ እንዲከላከሉ በተሰጠው ብይን መሰረት ‘የጦር መሳሪያ የፀና ፍቃድ ሳይኖር የሚለውን ተከላክለዋል’ የሚል ነው።
በመጨረሻ ግን ጥፋተኛ የተባሉበት አንቀጽ የተላለፈው ቅጣትም የተጋነነ እና ህጉን ስርዓቱን የተከተለ አልነበረም ብለን ይግባኝ ብለን ነበር ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የአቶ ታዬ ጠበቃ በቀጣይ ወደ ሰበር ይግባኝ የምንሄድ ይሆናል
Date:
