የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በፋይዘር ጌት የህግ ጉዳይ በሁሉም ክሶች መሸነፉ ተገለጸ

Date:

በኮቪድ-19 ክትባቶች ግዥ ላይ በኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት እና በፋይዘር ዋና ስራ አስፈፃሚ መካከል የጽሑፍ መልዕክቶች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ተዛማጅ እና ተከታታይ መረጃዎችን ኒው ዮርክ ታይምስ እንዳቀረበ በፍርድ ቤት ተረጋግጧል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን እና በፋይዘር ዋና ስራ አስፈፃሚ አልበርት ቡርላ መካከል የተለዋወጡ የጽሁፍ መልዕክቶች ማጋለጡን ተከትሎ፤ ስለ ጉዳዩ የተጠየቀዉ የአውሮፓ ህብረት ስራ አስፈፃሚ መልዕክቶቹን ያልያዘበትን ምክንያት በትክክል ማስረዳት አልቻለም ብሏል፡፡

በፋይዘር የCOVID-19 የክትባት ኮንትራቶች ዙሪያ በአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን እና በኒው ዮርክ ታይምስ መካከል ለረጅም ጊዜ ክርክር ሲነሳ ቆይቷል፡፡

የአውሮፓ ፍትህ ፍርድ ቤት ኮሚሽኑ “የተጠየቁትን ሰነዶች አለመያዙን ለማረጋገጥ አሳማኝ ማብራሪያ አልሰጠም” ሲል ዉሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ፤ኮሚሽኑ የተጠየቁትን ሰነዶች አልያዝኩም ማለት አይችልም፡፡ስለዚህ ሰነዶቹ ለምን ሊገኙ እንደማይችሉ ህዝቡም ሆነ ፍርድ ቤቱ እንዲረዱ የሚያስችል አስተማማኝ ማብራሪያ መስጠት አለበት ብሏል፡፡

በኮቪድ-19 ክትባቶች ግዥ ላይ በኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት እና በፋይዘር ዋና ስራ አስፈፃሚ መካከል የጽሑፍ መልዕክቶች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ተዛማጅ እና ተከታታይ መረጃዎችን ኒው ዮርክ ታይምስ እንዳቀረበ ፍርድቤቱ አረጋግጧል።

ከውሳኔው በፊት አንድ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣን፤ እነዚህ ውሎች ከዚህ በፊት ፈጽሞ ታይተው የማያውቁ ነበሩ ብለዋል።

ኒዉ ዮርክ ታይምስ በ 2021 ከዋና ስራ አስፈጻሚዉ ጋር በተደረገ ቃለ ምልልስ የመልዕክቶቹን መኖር አስታዉቆ የነበር ቢሆንም፤ህብረቱ መረጃዎችን ሲጠየቅ ጽሑፎቹን ማቅረብ አልችልም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

መልዕክቶቹን ለማግኘት ተደጋጋሚ ያልተሳካ ሙከራ ካደረገ በኋላ፤ኒው ዮርክ ታይምስ ጉዳዩን በጥር 2023 ለአዉሮፓ ፍትህ ፍርድቤት አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱ ፤ኮሚሽኑ የተጠየቁት የጽሑፍ መልዕክቶች መሰረዛቸውን አልያም ከተሰረዙም ሆን ተብሎ ወይም ባለማወቅ የተከሰተ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ማብራራት አልቻለም ሲል ወስኗል፡፡

በዉሳኔዉ ላይ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለፍትህ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት ሁለት ወራት አለው ሲል ዩሮ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...