የአፍሪካ ህብረት ለስምንተኛ ጊዜ ለተመረጡት ፖል ቢያ የደስታ መልዕክት አስተላለፈ

Date:

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሐመድ አሊ ዩሱፍ እ.አ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2025 በካሜሩን በተካሄደው ምርጫ ለስምንተኛ ጊዜ ለተመረጡትና ሀገሪቱን ለ43 ዓመታት ለመሩት አዛውንቱ ፕሬዝደንት ” በማሸነፍዎ ደስ ብሎኛል ” ሲሉ የደስታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ፕሬዝደንቱ በማሸነፋቸው ደስታቸውን ይግለጹ እንጂ በሀገሪቱ የተቀሰቀሰው ሁከት፣ የተቃዋሚዎችና ከምርጫው ውጤት ጋር ግንኙነት ያላቸው የፖለቲካ ተዋንያን እስርና አፈና ግን እጅጉን አሳስቦኛል ብለዋል።

በካሜሩን ሰላም እንዲሰፍንና ወደ መረጋጋቷ እንድትመለስ ሁሉም የፖለቲካ ተዋንያን ተቋማዊ በሆነ መልኩ አወንታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዩሱፍ፣ ፖል ቢያ ምርጫውን ቢያሸንፉም ሁሉን አካታች የውይይት መድረክ እንዲያዘጋጁ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የ92 ዓመቱ አዛውንት ፖል ቢያ፣ በተያዘው የጥቅምት ወር እንዳሸነፉ የተነገረለትን የስልጣን ዘመን ሲጨርሱ አንድ መቶኛ ዓመታቸውን ይደፍናሉ።

የዕድሜያቸውን እኩሌታም በፕሬዝደትነት አሳልፈዋል እንደማለት ነው።

መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ግን የደስታ መልዕክቱን አስተላልፏል።

(አዲስ_ማለዳ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...