አርሶ አደሩ የግብርና ምርቶቹን በንግድ እሳቤ ቢያመርታቸው አዋጭ እንደሚሆን  ተገለፀ

Date:

ለግብርናው በተሰጠው ዝቅተኛ ቦታ እና በህዝቡም በኩል ባለ የግንዛቤ ችግር  የተነሳ ከሺ አመታት በፊት በሚከናወንበት  አሰራር ዛሬም እርሻ በበሬ ይታረሳል ሲሉ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ የነበራቸዉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

የምጣኔ ሃብት ባለሞያና  በግብርና ጥናቶች ላይ ተትሳትፎ ያላቸው አቶ ይርጋ ተስፋዬ ለግብርናዉ ዘርፍ አለማደግ በቀዳሚነት የሚነሳዉ ችግር ለግብርናው ዘርፍ የሚመደበው የውጭ ምንዛሬ በቂ አለመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡

አቶ ይርጋ ተስፋዬ፤ የህዝቡም በግብርና ላይ ያለው ዝቅተኛ አመለካከት ዘርፉ ላይ እድገት መጠበቅ ያስቸግራል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማህበር ሲኒየር ሪሰርቸር የሆኑት ዶክተር  ሞላ አለማየሁ በበኩላቸዉ፤ ግብርና የኢትዮጵያ ሁሉ ነገር ሆኖ እያለ  በዘርፉ ላይ ለመሰማራት በባለሃብቶችም በኩል ያለዉ ግንዛቤ አነስተኛ ነዉ ብለዋል፡፡

ግብርናው በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ እንዳለው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በሳይንሳዊ መንገድ አለመመራቱንም ለዘርፉ ያለማደግ አንዱ ምክንያት ነዉ ሲሉ ዶክተር ሞላ አለማየሁ አስረድተዋል፡፡

ሆኖም ግብርናውን ለማሳደግ  የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ እቅድና ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ገልጸዉ፤በአብዛኛው የግብርና ዘርፉ የዝናብ ጥገኛ  እንደመሆኑ  ለዚህም መፍትሄ ማዘጋጀት ይገባል ሲሉ  ዶክተር  ሞላ አለማየሁ  ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሌላው አርሶ አደሩ ግብርናን ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ  አስፍቶ አለመመልከቱ ለግብርናው  አለማደግ ችግር ነው ያሉት አቶ ይርጋ ተስፋዬ አርሶአደሩ የግብርና ምርቶቹን በንግድ እሳቤ ቢያመርታቸው አዋጭ እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡
Ethio fm

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...