የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአዳማ-አዋሽ ፍጥነት መንገድ ሁለት ምዕራፍ ድጋፍ አቀረበ

Date:

የገንዘብ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ–ጅቡቲ–ደቡብ ሱዳን ትራንስፖርት ኮሪዶር ፕሮጀክት – ምዕራፍ IIን ለመደገፍ የሚያስችል የ184 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የዕርዳታ ስምምነት መፈራረማቸው ተገልጿል።

ገንዘቡ በአዲስ አበባ–ጅቡቲ ኮሪዶር ላይ ወሳኝ የሆነውን የ67 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ከመልካ ጂሎ እስከ አዋሽ ድረስ ለመገንባት ያስችላል ተብሏል።

ይህ መስመር ከ90% በላይ የሚሆነውን የኢትዮጵያ የባህር ንግድ የሚይዝ በመሆኑ ለሀገሪቱ የሎጂስቲክስ ፍሰት፣ ለክልላዊ ትስስር እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የኢኮኖሚ ውህደት ለማጠናከር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተመላክቷል።

ከሳምንታት በፊት የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን በሦስቱ ሀገራት መካከል የንግድ ልውውጥን፣ ትስስርን እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን እንደሚያሳድግ የሚጠበቀው የክልላዊ ውህደት መሪ ፕሮጀክት የሆነውን የደቡብ ሱዳን – ኢትዮጵያ – ጅቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍን ለማስጀመር 214.47 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማፅደቁ ይታወቃል።

የገንዘብ ድጋፉ ከአፍሪካ ልማት ባንክ በዝቅተኛ ወለድ መጠን የተገኘ ሲሆን ለኢትዮጵያ 181.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ለጅቡቲ 29.71 ሚሊዮን ዶላር እና ለደቡብ ሱዳን 1.96 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን የእርዳታ ድጎማዎችን እንደሚያካትት ካፒታል ዘግቦ ነበር።

ይህ ሁለተኛ ምዕራፍ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ፣ የ67 ኪሎ ሜትር ፈጣን መንገድ ግንባታን እና የትራፊክ አስተዳደርን የሚያሻሽሉ ዘመናዊ የትራንስፖርት ስርዓቶች መዘርጋትን እንደሚደግፍ ተገልጿል። እንዲሁም ለገጠር ማህበረሰቦች ተደራሽነትን ለማሳደግ 50 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ የአካባቢ መንገዶችን ያሻሽላል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...