የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ስራ እንደሚጀምር አስታወቀ። አየር መንገዱ ወደ ያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ በሳምንት ሶስት በረራዎችን ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።
በ83.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያ 45 ሜትር ስፋት እንዲሁም 2.6 ኪሎ ሜትር የማኮብኮቢያ ሜዳ ያለው ሲሆን በሚኖረው ወቅታዊ የንፋስ አቅጣጫ መነሻነት በሁለት አቅጣጫ አገልግሎት መስጠት የሚችል ሆኖ የተገነባ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታል።
የቦረና ዞን ህዝብ የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄ ሆኖ የኖረው የያቤሎ አየር ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት በ #ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በ #ቦርና ዞን ያቤሎ ወረዳ ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም መጀመሩም ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 21 የሀገር ውስጥ አየር ማረፊያዎች ያሉ ሲሆን ተጨማሪ የ5 አየር ማረፊያ ግንባታዎች በቀጣይ ወራት ተጠናቅቀው አገልግሎት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
