የኢትዮጵያ ብር በሩሲያ የባንክ ምንዛሬ ተመን ወጣለት

Date:

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ሌሊት ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ የኢትዮጵያን ብር በምንዛሬ ዝርዝር ውስጥ አካቷል።

ይህም ማለት ብርን ወደ ሩብል እንዲሁም ሩብልን ደግሞ ወደ ብር መመንዘር የሚያስችል ዕድልን ይሰጣል።

በዚህም መሰረት ባንኩ ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.5872  ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.575872 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።

ባንኩ ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ ይሆናል።

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...