የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ከዓድዋ ማግስት የተገኘው የአፍሪካ የኩራት አሻራ ነዉ

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ80 ዓመታት የከፍታ ጉዞ የማጠቃለያ መርሃ-ግብር ተከናውኗል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተቋሙን ከታላቁ የዓድዋ ድል ጋር በማስተሳሰር፣ የአፍሪካውያን የትስስር ድልድይ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ላለፉት ስምንት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያን ስም በዓለም ሰማይ ላይ ከፍ አድርጎ የሰቀለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ዛሬ ላይ የሀገር ግንባታና የጽናት ተምሳሌትነቱ በላቀ ድምቀት ተመስክሮለታል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ ከዓድዋ ድል ቀጥሎ አፍሪካውያንን በአንድነት ያቆመና ኩራትን የቸረ ተቋም ነው።

እንደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ተቋማት የሌሏት ሀገር ምሰሶ እንደሌለው ቤት ናት።

አየር መንገዱ ግን በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፎ፣ ትውልድን ከትውልድ በማገናኘት እንደ ወርቅ ነጥሮ የወጣ የሀገር ዓምድ ሆኗል።

ይህ ስኬትም ኢትዮጵያ ለጀመረችው የተቋማት ግንባታ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው፤ ተቋሙ ላለፉት 80 ዓመታት የገጠሙትን ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የተቋቋመበትን ጥንካሬ አውስተዋል።

በተለይም መላው ዓለም በአቪዬሽን ዘርፍ ተስፋ በቆረጠበት የኮቪድ-19 ወቅት፣ አየር መንገዱ ያሳየው ልዩ የመላመድ ብቃትና ያስመዘገበው ትርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚጠቀስ የጥንካሬ መገለጫ ሆኖ አልፏል።

በመድረኩ ላይ በስፋት የተነሳው ሌላው ነጥብ፤ የአየር መንገዱ የቀጣይ ጉዞ ነው። አሁን ላይ ተቋሙ የ2040 ራዕዩን ሰንቆ የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማስፋት እየተጋ ሲሆን፣ የቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታም የዚሁ አዲስ ምዕራፍ ማሳያ ተደርጎ ተቆጥሯል።

ከኢኮኖሚ አበርክቶው ባሻገር፣ አየር መንገዱ ያለፈበትን ታሪክ ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል ቋሚ የአቪዬሽን ዐውደ ርዕይ እንዲዘጋጅም ጥሪ ቀርቧል።

ይህም የወደፊት ባለሙያዎችን ልብ የሚቀሰቅስና የተቋሙን ግዝፈት በቋሚነት የሚያሳይ እንደሚሆን ታምኖበታል።

በአጠቃላይ የ80ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአህጉሪቱ ስኬት መሆኑ ዳግም የተረጋገጠበት ሆኖ ተጠናቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

 የ2026 የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ ሆኑ!

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓሪስ ውጪ በለንደን በተካሄደው ታላቅ የሽልማት...

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...