ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቻይናው ዳይመንድሊግ የድል መድረኩን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት

Date:

በቻይና ሺያመን በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ የወንዶች 5000 ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ይሁኔ አዲሱ 12፡57.32 በሆነ አስደናቂ ሰዓት አንደኛ በመውጣት አሸንፏል።

አትሌቱ ያስመዘገበው ይህ ውጤት የዓመቱ የዓለማችን ፈጣኑ ሰዓት ከመሆኑም በላይ የውድድሩ አዲስ ክብረ ወሰን  ሆኖ ተመዝግቧል።

በዚሁ እጅግ አጓጊ ውድድር ላይ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ድሉን ያደመቁ ሲሆን፣ አብዲላሂ መሀመድ በ12፡57.90 ሁለተኛ እንዲሁም ቢኒያም መሀሪ በ12፡58.51 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የድሉን መድረክ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ባንዲራ አሸብርቀውታል።

በሌላ በኩል ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት የኬንያ አትሌቶች በውድድሩ ላይ ጠንካራ ፉክክር ቢያደርጉም  ያሰቡትን ውጤት ሳያሳኩ ቀርተዋል።

ኤድዊን ኩርጋት ውድድሩን በ5ኛ ደረጃ ሲያጠናቅቅ፣ ከ2020 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ርቀት የተወዳደረው ታዋቂው አትሌት ጢሞቲ ቼሩዮት ግን ሳይሳካለት ቀርቶ በ12ኛ ደረጃ ለማጠናቀቅ ተገዷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...