የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረጉ በረራዎችን አስቆመ

Date:



‎በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የአየር ክልል መዘጋቱን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቀጠናው የሚደረጉ በረራዎችን ላልተወሰነ ጊዜ መሰረዙን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

‎አየር መንገዱ በረራ ካቋረጠባቸው መዳረሻዎች መካከል ኦማን፣ ቤይሩት፣ ባህሬን፣ ቴል አቪቭ፣ ዶሃ፣ ኩዌት፣ ዱባይ፣ ሻርጃህ፣ አቡ ዳቢ እና ዳማም ይገኙበታል።

‎ ኩባንያው ውሳኔውን ያስተላለፈው መንገደኞች ለተጨማሪ እንግልት እንዳይዳረጉና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል መሆኑን ገልጿል።

‎በረራ በተሰረዘባቸው መስመሮች ላይ ትኬት ለቆረጡ መንገደኞችም አየር መንገዱ ሦስት አማራጮችን ያቀረበ ሲሆን እነሱም በረራዎች ዳግም ሲጀምሩ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በሌላ ቀን መጓዝ፤ ጉዞን ወደ አቅራቢያ መዳረሻዎች ማዞር እና ጥቅም ላይ ላልዋለ ትኬት ሙሉ ክፍያን ተመላሽ ማድረግ ናቸው።

‎አየር መንገዱ የቀጠናውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ጠቅሶ፣ ለተፈጠረው መስተጓጎል ለደንበኞቹ ይቅርታ ጠይቋል።

መንገደኞች ወደ አየር ማረፊያ ከመሄዳቸው በፊት የበረራቸውን ሁኔታ በአየር መንገዱ የዲጂታል አማራጮች እንዲያረጋግጡም ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...