የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት በፖታሽ ማዕድን ልማት ላይ ለመሰማራት ተስማማ

Date:

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና የማዕድን ሚኒስቴር በሀገሪቱ ያለውን ሰፊ የፖታሽ ማዕድን ሀብት በጋራ ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የሆልዲንግሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና የማዕድን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) የፈረሙት ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም ለዘመናት ሳይለማ የቆየውን የፖታሽ ክምችት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በመቀየር የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ እና የግብርና አቅም ማሳደግ ነው።

ብሩክ ታዬ በወቅቱ እንደገለጹት፣ ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ ያላትን የፖታሽ ሀብት ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብና ለማዳበሪያ ምርት ግብዓትነት ለመጠቀም ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

በተለይም ማዕድኑን አጥሮ ከመያዝ ይልቅ በአግባቡ ወደ ስራ የሚያስገቡ ኩባንያዎች ላይ ትኩረት ለሚያደርገው አዲሱ ስትራቴጂ ሆልዲንግሱ ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወት አረጋግጠዋል።

የማዕድን ሚኒስትሩ በበኩላቸው፣ በአፍሪካ ግዙፍ ከሆነው የሉዓላዊ ሀብት ፈንድ ጋር አብሮ መስራት የማዕድን ዘርፉን ለማሳደግ ስልታዊ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ይህ ትብብር የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት በኃላፊነት ስሜት በማልማት ለረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ እድገት መሰረት ለመጣል ያለመ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...