ቡድኑ ነገ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር የመልስ ጨዋታውን ከዛምቢያ አቻው ጋር ያደርጋል።
የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በዛምቢያ የ 2ለ1 አሸናፊነት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።
ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኑ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ባደረገው የመጨረሻ ልምምድ :-
- የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳኛቸው ንግሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሪት ብዙዓየሁ ጀምበሩ እና የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል።
የኢትዮጵያ እና ዛምቢያ የመልስ ጨዋታ ነገ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል።
የጨዋታው የስታዲየም መግቢያ በነፃ ሲሆን ስፖርት አፍቃሪው ተገኝቶ ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያበረታታ ጥሪ ቀርቧል።
