የኢትዮጵያ የመድኃኒት ገበያ እስከ 2026 መጨረሻ 1.8 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል

Date:

የኢትዮጵያ የመድኃኒት ገበያ እ.ኤ.አ በ2026 ማጠቃለያ ላይ እስከ 1.8 ቢሊዮን ዶላር ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ነው።

የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ እንደገለጹት፣ ይህ ዕድገት ሊመዘገብ የሚችለው ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመድኃኒት ዘርፉ ላይ ሲካሄዱ የቆዩ ሰፋፊ ማሻሻያዎች ውጤት በማስመዝገባቸ ነው።

በተለይም ለሀገር ውስጥ ምርቶች ልዩ ትኩረት በመስጠትና አማራጮችን በማስፋት እየተከናወነ ያለው ሥራ ለገበያው ዕድገት ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ተመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቶ 40 በመቶ መድረሱን ዋና ዳይሬክተሯ አረጋግጠዋል። ይህም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ከመቀነስ ባለፈ በኢኮኖሚው ላይ የጎላ ፋይዳ እያበረከተ ይገኛል።

የመድኃኒት ግብይቱ እ.ኤ.አ በ2026 መጨረሻ ላይ ከ1.6 እስከ 1.8 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ መገመቱ ዘርፉ ያለውን ትልቅ የመልማት አቅም የሚያሳይ እንደሆነም ተገልጿል።

ይህንን ግዙፍ የገበያ ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ባለሥልጣኑ የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችን ከማበረታታት ባለፈ ከጤና ሚኒስቴርና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራ ተገልተጾአል።

በተለይም ጥራቱን የጠበቀ የመድኃኒት አቅርቦት ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና በዘርፉ የሚታዩ የአቅርቦት ክፍተቶችን ለመሙላት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዳይሬክተሯ በሰጡት ማብራሪያ አመልክተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...