የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ይዞታ እና የኢትዮጵያና ኤርትራ የቃላት ውዝግብ ያሳደረው ስጋት

Date:



የትግራዩ ጦርነት ካበቃ ሦስት ዓመት ቢጠጋም ትግራይአሁንም ለጋዜጠኞች አደገኛ መሆኗ ቀጥሏል ሲል ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ ትናንት አስታውቋል።

CPJ በተለይ ለተተኮሰባቸው፣ ለታሰሩ ድንገተኛ አሰሳም ለተካሄደባቸውና በአካባቢው እንደገና ግጭት ሊያስነሳ የሚችል የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ ለሚዘግቡት ጋዜጠኞች ክልሉ ውጥረት የሰፈነበትና አደገኛም ነው ብሏል። CPJ ከዚህ ቀደም በአጠቃላይ  በኢትዮጵያ አለ ያለውን የፕሬስ ነጻነት ገደብም ሲያወግዝ ቆይቷል።


በሌላ በኩል የቃላት ውዝግብ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ሌላ ግጭት በመግባት ተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይደርሱ  የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

 CPJ ትግራይ ክልልን ለጋዜጠኞች አደገኛ ስለማለቱ ፣ ስለኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ይዞታ እናበኢትዮጵያ እና በኤርትራ አንዣቧል ስለተባለው የዳግም ግጭት ስጋት  የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል ሃላፊ አቶ ያሬድ ኃይለማርያምን በስልክ አነጋግረናቸዋል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...