የኢጣሊያና ኢትዮጵያ የሕዋ ሳይንስ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ

Date:

​በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የኢጣሊያ ምርምር ቀንን (GRIM) ምክንያት በማድረግ፣ በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል ያለውን የሕዋ ሳይንስ ትብብር የሚያጠናክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ትናንት ተካሂዷል።

በታሪካዊው ፖስታ ቤት የፈጠራ ማዕከል (Creative Hub) በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ የሁለቱ አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የተመራማሪዎች ቡድን እና የቪላ ኢጣሊያ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

​በጉባኤው ላይ የተፈጥሮ አደጋዎችን መከላከል እና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የኢጣሊያ አምባሳደር ሴም ፋብሪዚ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለት ሳተላይቶችን ወደ ሕዋ ማምጠቋ በዘርፉ ያላትን ተነሳሽነት ያሳያል።

​ይህ የሁለት ቀናት መርሃ ግብር በASI እና Telespazio የተዘጋጀውን “Looking Beyond” የተሰኘ አውደ ርዕይ ያካተተ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹ በ3,000 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኘውን የእንጦጦ የሕዋ ምርምር ማዕከልን በመጎብኘት አጠናቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...