ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱን ለማስቆም የሚያስችለው ስምምነት “ዛሬ ዕሁድ “ ይፈረማል አሉ።
ኢራን ግን የተቀመጠውን ቀነ ገደብ እንደማትቀበለው ያስታወቀች ሲሆን ዛሬ ከሚለው ይልቅ በመጭዎቹ ቀናት በሚለው ላይ ተስማምታለች የሚል መረጃም ወጥቷል።
ትራምፕ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የሆርሙዝ ሰርጥ በአንድ ጊዜ ለሁሉም ክፍት ይሆናል በሚል ሀሳባቸውን ገልፀዋል።
የኢራንን ዩራኒዬም አሜሪካ እንደምታገኘውም አያይዘው አስታውሰዋል ትራምፕ።
በዕርግጥ ሪፐብሊካኑ የድርድሩን ስርዓት ትርክት በራሳቸው መንገድ ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው በሚልም ተወቅሰዋል።
በሌላ በኩል የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ አባስ አራግቺ እንዳይንቀሳቀስ የተያዘው ሀብታችን በሂደት መለቀቅ አለበት ብለዋል።
በደቡባዊ ሊባኖስ እስራኤል ጥቃቷን አጠናክራ መቀጠሏ ደግሞ ለመግባቢያ ሰነዱ ፊርማ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችልም እየተነገረ ነው።
ኢስላማባድ ፓኪስታን የፊርማ ስነ – ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ እንደሚሆንም ማሳወቋም አይዘነጋም።
ዘገባው የሲ ኤን ኤን
