የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት የገቢ ማሰባሰቢያ ሪከርድ በመስበር ተጠናቀቀ

Date:

ከመጋቢት 11 እስከ መጋቢት 12/2018 በእንጦጦ ኪዳነምሕረት አዳራሽ ሲከናወን የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር 170,000,000.000 /አንድ መቶ ሰባ ሚሊያን/ ብር በመሰብሰብ ተጠናቀቀ።

ከዚኽ ውስጥ 139,000,000.00 ሚሊዬን ብር የተረጋገጠ ሲሆን ቀሪው 31 ሚሊዬን ብር ደግሞ ቃል የተገባ ሲሆን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

ይኽንን መርሐግብር ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ መልአከ አሚን ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ይርሳው የገዳሟ ዋና አበመኔት፣ ማኅበረ መነኮሳቱ፣ ማኅበረ መነኮሳቱ፣ መምህራን፣ ዘማርያን፣ ምእመናን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሦስቱንም ሌሊት በንቃት ተሳትፈውበታል።

ቲክታከሮች፣ ዩቱበሮች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ዶክመንተሪ፣ ማስታወቂያ፣ ቀጥታ ሥርጭት መርሐግብሩን በትሩፋት በማገልገላቸው ከገዳሟ አበው መነኮሳት ማስታወሻ እንዲኾናቸው መንበሯ ላይ ያለችውን የድንግል ማርያም ሥዕለ አድኅኖ እና ሠርተፍኬት በስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ይኽንን ኹነት ከኮሚቴው ጋር በመተባበር የማስተባበር እና የማማከር ተግባር ለአንድ ወር ያከናወነው ሎዛ ኹነቶች – Loza Events በትሩፋት በማገልገሉ መንበሯ ላይ ያለችውን የድንግል ማርያም ሥዕለ አድኅኖ፣ የወርቅ ካባ እና ሠርተፍኬት ከብፁዕ አቡነ መቃርዮስ እና ከገዳሙ አበመኔት እጅ በስጦታ ተበርክቶለታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...