የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዲዬር ሊየን የኢራኑን ጦርነት ለመቋጨት ድርድር እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ።
የቀጠለው ጦርነት እጅጉን አሳስቦኛል ብለዋል ቮን ዲዬር ሊዬን።
በድርድር ላይ መሰረቱን ያደረገ ሰላም መምጣት እንዳለበት ያስገነዘቡት ሀላፊዋ የሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባም አስጠንቅቀዋል።
ጦርነቱ ሲጠናቀቅ የአውሮፓ አገራት ሆርሙዝን በመጠበቁ ተልዕኮ ለመሳተፍ እና ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውንም በካንቤራ አውስትራሊያ ከጠቅላይ ሚኒስትረ አንቶኒ አልባኔዝ ጋር ሆነው ጠቁመዋል።
ጫናውን በነዳጅና ጋዝ እንዲሁም በንግድ ስራዎቻችን ላይ እያስተዋልን ነው ያሉ ሲሆን የከፋ ቀውስ ሳይፈጠር አማራጭ መፈለግ ወሳኝ እንደሆነም ተናግረዋል።
በህዝባችን እና በነዳጅ ዋጋ መጨመርም ፈተና ላይ ነን ብለዋል ቮን ዲዬር ሊዬን።
ሆርሙዝ ለአውሮፓ አጋሮች በዓለም ዙሪያ ቁልፍ የኢነርጂ አቅርቦት ሰርጥ መሆኑን እና ለበርካታ እንቀስቃሴዎች ሚናው የዋዛ አለመሆኑንም አስምረውበታል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
NBC Ethiopia
