የዘንድሮው የፀረ-ትምባሆ ቀን በዓለምለ38ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ “አማላይ ምርት፣ ለድብቅ ዓላማ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።
ይህም የትምባሆ እና የኒኮቲን ኢንዱስትሪዎች የሚጠቀሙባቸውን ድብቅ ዘዴዎች ለማጋለጥ ያለመ ነው።
የትምባሆ እና የኒኮቲን ኢንዱስትሪዎች እንደ ማራኪ የምርት ንድፎች፣ግሩም ጣዕሞች እና ውብ የሆኑ የግብይት ዕቃዎችን በመጠቀም ወጣቶችን ዒላማ በማድረግ አደገኛ ምርቶቻቸውን በድብቅ ለማሠራጨት ይሠራሉ።
በተለይም ‘ኢ-ሲጋሬት’ የተባለው እና በጣፋጭ ከረሜላ መልክ የሚዘጋጁየትምባሆ ዓይነቶች በርካቶችን ተጋላጭ እንዳደረጉ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።
እንደ ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ13-15 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 37 ሚሊየን አዳጊዎች በዚሁ ስልትተታልለው ትምባሆ እንደሚጠቀሙ ኢቢሲ ዘግቧል።
በምሥራቅ ሜዲትራኒያን የዓለም ክልል በሚገኙ አንዳንድ ሀገራት አጫሽ የሆኑ አዳጊ ወንዶች (ከ13-15 ዓመት ዕድሜ) 43 በመቶ ሲሆን አጫሽ የሆኑ አዳጊ ሴቶች ቁጥር ደግሞ 20 በመቶ ደርሷል።
ትምባሆ የማህፀን በር ካንሰር እና የመራባት ችግርን ጨምሮ ሌሎችየጤና አደጋዎችን ያስከትላል።
የዓለም የፀረ-ትምባሆ ቀን የትምባሆን ተፅዕኖ ለመዋጋት ያለመ ዓለም አቀፍ ንቅናቄ ነው።
የዓለም ጤና ምክር ቤት በፈረንጆቹ 1987 ዓ.ም ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የዓለም የፀረ-ትምባሆ ቀን በ1988 ለመጀመሪያ ጊዜግንቦት 23 ቀን ነበር በመደበኛነት መከበር የጀመረው።
