የፓርቲው መሥራች አባል ከሆኑት ውስጥ 100 ያህሉ ከህወሓት የወጡ ናቸው

Date:

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራውና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ያገኘው አዲሱ ‘ዴሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ’፤ መመስረቻ ጉባኤውን በዚህ ዓመት በትግራይ ክልል እንደሚያካሄድ አስታውቋል፡፡

ፖርቲው ዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም የመጀመሪያውን ጋዜጣዊ መግለጫውን በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ያካሄደ ሲሆን፤ በመግለጫውም ግዜያዊ ፍቃድ ከምርጫ ቦርድ ማግኘቱን ገልጿል፡፡

አዲሱ ፖርቲ ‘በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ አካሄድ ወደ ተሳሳተ መንገድ በመሄዱና ለውጥ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ በመሆኑ፤ አዲስ እና የተለያየ ሀሳብ ያለው ፖርቲ ለመመስረት እንዳስፈለገ’ ገልጿል።

መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ እና የአደራጅ ኮሚቴ አባል አቶ ረዳኢ ኀለፎም፤ የፖርቲው መስራች የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በሕመም ምክንያት መግለጫው መስጠት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ዴሞክራሲ ስምረት ትግራይ ፖርቲ ‘ክልሉ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ውስጥ ይገኛል’ የሚል ሀሳብ በሁሉም ለውጥ ፈላጊ ላይ በማደሩ ምክንያት እንዲሁም፤ ‘ትግራይ አዲስ ለውጥ ያስፈልጋታል’ የሚል እምነት በመኖሩ የተፈጠረ አዲስ ፖርቲ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

ማንኛውም ‘ሀሳብ አለኝ’ የሚል ትግራዋይ የፖርቲውን ደንብና መተዳደሪያ የሚቀበል ከሆነለ ስምረትን መቀላለቀል የሚችል መሆኑንም በመግለጫው ተናግረዋል።

ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ፖርቲው ከክልል እስከ ቀበሌ አደረጃጀቶችን የመመስረት ሥራዎችና የአባላት ምልመላ ሥራዎች እንደሚሰራ የገለጹት አቶ ረዳኢ፤ “ከዚህ ቀደም የህወሓት አባል ሁኖ ለውጥ የሚፈልግ ካለም አባል መሆን ይችላል” ብለዋል።

“ከዚህ ውጪ የህወሓት አባል የሆኑ ወጣቶችን እንዲሁም ከትግራይ ውጪ ያሉ የትግራይ ተወላጆችም የፖርቲው አባል እንዲሆኑ ይሰራል” ሲሉም ገልጸዋል።

አክለውም “በህወሓት ውስጥ ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ አራት ግለሰቦች ‘ሠራዊቱን እናዛለን’ የሚል ዕምነት እንዳላቸው ስለሚያምኑ፤ ትግራይን ሰላም የነሷት መላው የህወሓት አባላት ሳይሆኑ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ውጪ ያሉና ሕገ-ወጡን ጉባኤ ያካሄዱት ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአሁን ወቅት የፓርቲው መሥራች አባል ከሆኑት ውስጥ 100 ያህሉ ከህወሓት የወጡ መሆናቸውና፤ ከእነዚህ ውስጥም ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት በትግራይ እንደሚነገኙም አቶ ረዳኢ ገልጸዋል፡፡

ፖርቲው በትግራይ የተለያዩ መድረኮች እንደሚካሄዱ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ክረምት ሳይወጣ በትግራይ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚካሄድም በመግለጫው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአቶ ጌታቸው ረዳ ለተመሠረተው አዲሱ የትግራይ ፓርቲ “ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ” (ስምረት) ፓርቲ፤ ጊዜያዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ ፈቃድ ባሳለፍነው ሳምንት መስጠቱ ይታወቃል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...