የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስራኤል ፖሊሶች በክርስቲያኖች ላይ ያደረሱትን ጥቃት እና በእየሩሳሌም በሚገኘው ቅዱስ የመቃብር ስፍራና ቤተክርስትያን በተቀደሰው ቅዳሜ እንዳገቡ መከልከላቸውን አውግዟል።
የሚኒስቴሩ ይፋዊ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዶ/ር ሱፊያን ኩዳህ በክርስቲያኖች ላይ የተወሰደውን ህገወጥ የእስራኤላውያን የእገዳ እርምጃዎችን በመቃወም ወደ ቅድስት መቃብር ቤተክርስትያን በነፃነት ሃይማኖታዊ ስርአታቸውን እንዳይፈጽሙ መከልከሏን በመንግስታቸው ዘንድ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው ሲል የሚኒስቴሩ መግለጫ ገልጿል። “እነዚህ እርምጃዎች በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ጊዜያዊ እና የቦታ ክፍፍልን ጨምሮ አዳዲስ እውነታዎችን ለመጫን በማሰብ በተባረከዉ አል-አቅሳ መስጊድ ወይም አል-ሀራም አል-ሸሪፍ ላይ የሚፈፀመውን ተደጋጋሚ ወረራዎች ጋር ይመሳሰላሉ” ሲሉ አምባሳደር ዶ/ር ሱፊያን ኩዳህ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የምግብ እና የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ ምንም አይነት እርዳታ በእስራኤል ጦር እገዳ የተነሳ ከ50 ቀናት በላይ እየገባ አይደለም፤ “ጋዛ አሁን ምግብ ትፈልጋለች” ሲል የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በኤክስ ላይ በለጠፈው ጽሁፍ አጋርቷል። የውሃ እጥረቱ እየተባባሰ መምጣቱን የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኦቻ በበኩሉ ገልጿል። የከባድ ማሽነሪዎች እና መሳሪያዎች እጥረት እንዲሁም የእርዳታ ሰራተኞች ግድያ የነፍስ አድን ስራ ላይ እንቅፋት ፈጥሯል ሲል ኦቻ አክሏል። የጋዛ ጤና ስርዓት በሆስፒታሎች ላይ በሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ወድሟል።
