የዱባይ የቅንጦት ሆቴል በኢራን ሚሳኤል ጋየ

Date:

​በዱባይ የሚገኘው ታዋቂው ‘ፌርሞንት ዘ ፓልም’ የቅንጦት ሆቴል በደረሰበት የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት አስተናገደ።

አደጋው የተከሰተው ኢራን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላይ በሰነዘረችው የሚሳኤል ጥቃት ወቅት የተተኮሱ ሚሳኤሎች ተመተው ሲወድቁ ባረፉ ፍንጣሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

​አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ “ኤፒክ ራዝ” እና “ላየንስ ሮር” የተሰኙ ጥቃቶችን መሰንዘራቸውን ተከትሎ፣ ኢራን በአጸፋው በዱባይ፣ ባህሬን እና ኳታር በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የመከላከያ ሚኒስቴር አዳዲስ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታውቋል።

​በአሁኑ ወቅት በዱባይ አየር ማረፊያዎች ተዘግተው ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ እየተደረገ ሲሆን፣ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ የት እንዳሉ አለመታወቁ በቀጠናው ያለውን ውጥረት ይበልጥ አባብሶታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...