ፕሬዚዳንቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአፍሪካ የምታደርገው ኢንቨስትመንት ወታደራዊ መስፋፋትን በውስጡ የያዘ ነው ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌህ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአፍሪካ የምታደርገው የ110 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት በኢኮኖሚ ልማት ሽፋን ወታደራዊ መስፋፋትን በውስጡ የያዘ ነው ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ሃገሪቷን አካባቢው እንዳይረጋጋ እያደረገች ነው ብለው ሲከሱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወደብ እና ቴሌኮሙኒኬሽን በመሳሰሉ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚታዩ አጋርነቶች ኢኮኖሚያዊ አንድምታ ሳይሆን ያላቸው የአፍሪካ ሃገራትን ሉዓላዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ወታደራዊ አላማዎችን የያዙ ናቸው ብለዋል።
የጂቡቲው ፕሬዚዳንት በተጨማሪ ከዚህ በፊት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በእኛ ወደብ ላይ ወታደራዊ ሰፈር ለመገንባት ጠይቃ ጥያቄዋን ስላልተቀበልን ትኩረቷን ወደ ጎረቤት ሃገሮች አድርጋለች ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በአካባቢው ኢኮኖሚን ከወታደራዊ ትብብር ጋር የቀየጡ አካሄዶች ስጋተ ናቸው ያሉ ሲሆን ሁኔታዎቹ የኛን ሉዓላዊነት እንዳይሸራርፉ በአትኩሮት እንከታተላለን ብለዋል።
ጂቡቲ በአሁኑ ወቅት እንደ አሜሪካ፣ቻይና፣ፈረንሳይ እና ጃፓን ላሉ ሃገራት ወታደራዊ ሰፈሮችን በባህሯ ላይ መስጠቷም ይታወቃል።
Source: All East Africa
