የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ የገቢ ግብር ረቂቅ ደንብ ማዘጋጀቱን አስታወቀ

Date:

አዲሱ መመሪያ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017ን ለማስፈጸም ያለመ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ነዋሪ ሆነው ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ምንጮች በዲጂታል አማራጮች ገቢ የሚያገኙ ግለሰቦችን በሙሉ የሚመለከት ነው።

ረቂቅ ደንቡ በተለይ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት የሚያገኙትን ገቢ በትክክል የሚገልጽ የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ እንደሚኖርባቸው ይደነግጋል።

ከዚህም በተጨማሪ ለፈጣሪዎቹ ክፍያ የሚያመቻቹ ኩባንያዎች ስለ ተከፋዮቹ ማንነትና የክፍያ መጠን በየሩብ ዓመቱ ለታክስ ባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል።

ሚኒስቴሩ ማንኛውም ፍላጎት ያለው አካል በረቂቁ ላይ ያለውን አስተያየት እስከ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በጽሑፍ ወይም በኢሜል እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርቧል።

ይህ እርምጃ በሀገሪቱ እያደገ የመጣውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ከነባሩ የግብር ሥርዓት ጋር ለማስተሳሰር የተወሰደ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...