ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ የጉምሩክ ቀረጥና ተጨማሪ ቀረጥ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር በግማሽ መቀነሱ ተገለጸ። ይህ ቅናሽ በዋናነት ከውጭ የሚገቡ የሸቀጦች መጠን እና ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት እንደሆነ ተጠቁሟል።
እኤአ 2015/16 ጀምሮ የነበረው የጉምሩክ ቀረጥና ተጨማሪ ቀረጥ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 2.1% የነበረ ሲሆን፣ ይህ አሃዝ በ2022/23 ወደ 1.0% ዝቅ ብሏል።
የዚህ መቀነስ ዋነኛ ምክንያት፣ ከውጭ የሚገቡ የሸቀጦች መጠን ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከ24% ወደ 10% በመውረዱ እንደሆነ የገንዘብ ሚኒስቴር የሰሞኑን ጥናት ያመለክታል።
ይህ የገቢ ቅናሽ አጠቃላይ የግብር እና የሀገር ውስጥ ምርት ጥምርታ መውረድ ውስጥ አንድ አራተኛውን ይዟል።
ከ2015/16 እስከ 2021/22 ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የውጭ ምርቶች መጠን መቀነስ በዋነኝነት በካፒታል ዕቃዎችና በኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃዎች ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በመቀነሱ ምክንያት ነው።
ሚኒስትሩ ከ የፊስካል ጥናት ተቋም (IFS) በጋራ ባዘጋጁት አዲስ ጥናት ላይ እንደገለፁት የውጭ ምንዛሪ እጥረት የውጭ ምርቶች ፍላጎትን በመቀነስ ለዚህ ለውጥ አስተዋጽኦ አድርጓል።
በ2021/22 እና በ2022/23 መካከል የውጭ ምርቶች እና የሀገር ውስጥ ምርት ጥምርታ መቀነስ በአብዛኛው በዋጋ ለውጦች ምክንያት መሆኑን ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።
CapitalNews
