የጣና በለስ የስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት

Date:

ለግንባታ ሚሊዮኖች ብር ከፈሰሰበት በኋላ ሥራ አቁሞ የተዘጋው የጣና በለስ የስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት እንዲመለስ የ850 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ፀድቆለታል ተባለ፡፡

ፋብሪካው በ2,000 ሄክታር ቦታ ላይ የአገዳ ልማት እየተከናወነለት መሆኑን ሰምተናል፡፡

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ይህ ሁሉ ድጋፍ ከተደረገለት በኋላ በ2018 ዓ.ም ማገባደጃ ወይም 2019 መግቢያ ምርት ማምረት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰምተናል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት  የአየር ጠባዩ የሚስማማ ውሀውም የተንጣለ ቦታ በመሆኑ ሌሎች የሰብል ምርቶችን ለማምረት ወደ ስራ ተገብቷል ተብሏል።

የጣና በለስ ስኴር ፋብሪካ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ በአመራር የተሻለ እንዲሆን በየደረጃው እየተደገፈ ነው ተብሏል።

ወሬውን የኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ(ዶ/ር) ነግረውናል።

ለዚህ ፕሮጀክት የተፈቀደው 850 ሚሊየን ብር ድጋፍ ደረጃ በደረጃ ስራዎች እየታዩ እና እየተቆጠሩ የሚለቀቅ መሆኑንም ሰምተናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...