የፋይዳ መታወቂያን በ”PDF” አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት መቋረጡን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡
የፋይዳ መታወቂያን በ”PDF” አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት የተቋረጠበት ምክንያት፡-
- በየአካባቢው የሚገኙ የኢንተርኔትና ሕትመት ቤቶች ጥራት በሌላቸው ካርዶች እያተሙ በመሆኑ፣
- የአንድን ግለሰብ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በፎቶሾፕ እያስመሰሉ በመስራት የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎችን እያጭበረበሩ ያሉ አታሚዎች በስፋት መታየታቸው፣
- ከከተማ ራቅ ብለው የሚኖሩና በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ዜጎች ትክክለኛ ባልሆነ የካርድ ሕትመት እየታለሉ ፤ ገንዘብና ጊዜያቸውን ከመጭበርበራቸው ባሻገር የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ እያደረገ በመሆኑ የሚሉት ናቸው፡፡
ስለሆነም ዜጎች የኢ-ፋይዳ አማራጭ ሲፈልጉ የ”Fayda ID” ሞባይል መተግበሪያ ላይ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጠቁሟል፡፡
