የ ሺ እና የትራምፕ ውይይት ተጠናቋል

Date:


ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጋር ያደረጉትን ውይይት አጠናቀው ደቡብ ኮሪያን ለቀው ወጥተዋል።

ትራምፕ ከሺ ጋር ጥሩ ውይይት ነበረን ከማለት በቀር እስካሁን ይፉ የሆነ ምንም አይነት የንግድ ስምምነት የለም።

ዶናልድ ትራምፕ ከውይይቱ በኋላ በኤርፖርት ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ መልካም የሚባል ውይይት ማድረጋቸውንና ፤ ጥሩ ውሳኔዎች ላይ መድረሳቸውን በግርድፉ ተናግረዋል።

በርካታ ጠቃሚ ነጥቦች ላይ ድምዳሜ አግኝተዋል በቅርቡም እናሳውቃችኋለን ብለዋል ትራምፕ።

በመጪው ሚያዚያ ወር ወደ ቻይና ሊያቀኑ እንደሚችሉም ፤ ከዛን በኋላ ሺ ወደ ዋሺንግተን ሊመጡ እንደሚችሉ ዶናልድ ትራምፕ ፍንጭ ሰጥተዋል።

በውይይታቸው ወቅት የታይዋን ጉዳይ ተነስቶ ከሆነ በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ትራምፕ በውይይታቸው ፈፅሞ የታይዋን ስም አለመጠቀሱን ገልፀዋል።

በዩክሬን ጉዳይ ላይ ቤጂንግና ዋሺንግተን በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል።

ቻይና በትላንትናው እለት ዳግም እንዲጀመር ያፀደቀችውን የአኩሪ አተር ምርት ከአሜሪካ መግዛት እንደምትጀምር ጠቁመዋል፤

የታሪፍ ቅናሽ አሁን ካለበት ምን አልባትም ከ57 እስከ 47 በመቶ ቅናሽ ሊደረግ እንደሚችል ከንግግራቸው የተገኘ መረጃ ይጠቁማል።

ከቤጂንግ ጋር በቅርቡ ይፉዊ ስምምነት ይኖረናል ብለዋል ትራምፕ።

በእስያ በነበራቸው ይፉዊ የስራ ጉብኝት የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሳያገኙ ቢመለሱም ዳግም እንደሚመጡና እንደሚያነኟቸው ገልፀዋል።

ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ጥሩ ወዳጅነት አለኝ ብለዋል ትራምፕ።

አልጀዚራ፣ ሲኤን ኤን፣ ቢቢሲ እንደዘገቡት።

NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አለሁ እኔ ለወገኔ የድጋፍ ጥሪ

እሺ ምን እናድርግ? አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች...

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ከፍተኛ የእይታ ችግር አለበት

በኢትዮጵያ ከ1.6 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕብረተሰብ ከፍተኛ የእይታ ችግር...

3ኛው የሩሲያ – አፍሪካ ጉባኤ በሞስኮ ይጀምራል

ጥቅምት 28 እና 29 እ.ኤ.አ.3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ...

ዳሸን ባንክ  “ዳሸን ኤር ፔይ” የተሰኘ  የክፍያ አገልግሎት አስተዋወቀ

  ዳሸን ባንክ ለንግድ ተቋማትና ለደንበኞች ግብይትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማከናወን...