የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው 

Date:

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ፥ ” ይሄ አራተኛው ነው በአዲሱ የፈተና አሰጣጥ ፈተና የሚሰጥበት ” ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከትምህርት ቤቶች ወጥቶ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስገብቶ ፈተና እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ስለዘንድሮው የ2017 ዓ/ም ፈተና በተናገሩበት ወቅት 150 ሺህ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይ እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) ፥ ” እንደ ከዚህ ቀደሙ አድካሚ በሆነ ከቦታ ቦታ ልጆችን እያዘዋወሩ ከመሄድ ባለፈው ዓመት 29 ሺህ ተማሪ ነበር ኦንላይን ፈተና የሰጠነው ዘንድሮ ደግሞ 150 ሺህ ተማሪ ኦንላይን ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጀን ነው ” ብለዋል።

ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ቆርጠው ባይናገሩም ፈተናው ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንዲሰጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...