የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሜ ሩጫ ውድድር ተካሄደ

Date:

‎የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ክቡር ሻለቃ ሀይሌገ/ስላሴ፣ ተምሳሌት አትሌቶች እና ሌሎች የክብር እንግዶች በተገኙበት የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የሩጫ ውድድር ተካሂዷል።

በውድድሩ በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ተምሳሌት ሴቶች፣ ሴት አምባሳደሮች፣ ሴት አትሌቶች ና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰሩ ሴት ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል::

በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ በሚል መርህ ቃል የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ በዛሬ እለት መነሻ እና መድረሻውን ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ በማድረግ የተካሄደ ሲሆን 23ኛ ዓመቱ ላይ የደረሰው ይህ ውድድር ዘንድሮም 16 ሺህ ሴቶች የተሳተፉበት ውድድር ነው ተብሏል።

በዚህ በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ በሚል መርህ ቃል በተካሄደዉ የዘንድሮ ዉድድር ከ150 በላይ ጠንካራ አትሌቶችን አፎካክሮ በአምናዋ የመድረክ ባለድል የበላይነት ተጠናቋል።

በ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር፤ የአካል ጉዳተኞች የዊልቼር ውድድርም ተካሂዷል።

የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሜ ውድድር የሴቶችን ስኬት እየዘከረ ፣ ሴቶች ለሰሯቸው ስራዎች ዕውቅና እየሰጠ እና ሴቶችን በስፖርት ጤናማ እንዲሆኑ እያበረታታ 23 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ንባብ ለህይወት!” ታላቅ የንባብ ሳምንት እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት እና የንባብ ለህይወት...

በኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ

በኢትዮጵያ ከ10 ሚልዮን በላይ ሰዎች ከሄፓታይተስ ቢ እና ከ2...

የቶዮታ ኮሮላ መኪና በኤሌክትሪክ ሊመጣ ነዉ

የዓለማችን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆነው ቶዮታ፤ እንደ ቴስላ እና...

ኢራንን ለመምታት የዩናይትድ ስቴትስ ጄቶች ከምድሯ ይነሱ እንደነበር እሥራኤል ይፋ አደረገች

የእሥራኤል መከላከያ ሚንሥትር እሥራኤል ካትስ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች...