ዩክሬን ተዋጊ ጀት ገዛች

Date:


የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አንድ መቶ የጦር ጀቶችን ለመግዛት መፈራረማቸው ተገለፀ ።

የጦር መሳሪያ ፍለጋ ወደ ፈረንሳይ ያቀኑት ዘለንስኪ ፣ ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ለቀጣይ አስር ዓመት የጦር መሳሪያ ስምምነት አድርገዋል ።

የዘለንስኪ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፣ ፈረንሳይ እና ዩክሬን ፣ ፓሪስ አጠገብ በሚገኘው ቪላኮብላይ የአየር ማዘዣ ላይ ዓላማ ተኮር አዋጅ (declaration of intent) የተሰኘ ስምምነት መፈራረማቸውን ነው።

እጅግ ታሪካዊ በተባለው በዚህ ስምምነት ፣ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሁለቱ ሀገራት በፀጥታ እና ሰላም ጉዳዮች በሚቻለው ሁሉ ለመተባበር በጋራ መቆም አለባቸው ብለዋል።

ዩክሬን ለረዥም ጊዜ የሚሆን ወታደራዊ አቅሟን ፍፁም አስተማማኝ በሆነ መንገድ ማጠናከር አለባት ሲሉም ማክሮን አክለዋል ።

ሁለቱ ሀገራት የጦር መሳሪያ ስምምነት እያደረጉ ባሉበት ሰዓት የሩሲያ ሀይሎች ወደ ምስራቅ ዩክሬን እየገሰገሱ መሆናቸው ታውቋል።

ኡፒ፣ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እና ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግበውታል ።

በ-ቶማይ መኮንን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...