ከተቋሙ እውቅና ውጪ ይፋ የሚደረጉ ቁጥራዊ መረጃዎችን በጥንቃቄ መመልከት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳሰበ

Date:

በተለያዩ ተቋማት ተጠንተው፤ ከድህነት ወለል፣ ከሕዝብ ቁጥር፣ ከዋጋ ግሽበት እና ከሌሎችም ጉዳዮች አንጻር ይፋ የሚደረጉ ሪፖርቶች የሚገለጹ ቁጥራዊ መረጃዎች፤ በጥንቃቄ መታየት እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳስቧል፡፡

መቀመጫቸውን ሀገር ውስጥ ያደረጉትም ሆነ በሌሎች የዓለም ሀገራት የሚገኙት አጥኚዎች ቁጥራዊ መረጃዎችን ለተመለከተ ጥናታቸው፤ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎትን ማማከር እንደሚገባቸው ያስታወሱት የተቋሙ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሳፊ ገመዲ ናቸው፡፡

ኃላፊው አክለውም፤ ተቋሙ ኢትዮጵያን በተመለከተ ያሉ ሕጋዊ የቁጥር መረጃዎችን የሚሰጥ በመሆኑ ከእውቅናው ውጪ ያሉ መረጃዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ከዋጋ ግሽበት፣ ከሕዝብ ብዛት፣ ከድህነት እና መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ይፋ የሚያደርጓቸው መረጃዎች የተጋነኑ እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ካለው መረጃ ጋር የተቃረነ የሚሆኑበት ጊዜ መኖሩንም ኃላፊው አቶ ሳፊ አንስተዋል፡፡

ለጥናት መነሻ የሚሆናቸውን መረጃ ከተቋሙ ያልተቀበሉና በራሳቸው መንገድ አጥንተው ቁጥራዊ መረጃዎችን ይፋ የሚያደርጉ ተቋማት የሚያሰራጩት መረጃ ትክክለኛ ያለመሆን ዕድል ስለሚኖረውም፤ ተገልጋዮች በመረጃው ከመገልገላቸው በፊት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘውም ቁጥራዊ መረጃዎችን የመስጠት ኃላፊነት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለስልጣን መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ጥናት ማድረግ የሚፈልጉ ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች የመነሻ መረጃውን ከተቋሙ መውሰድ እንደሚገባቸው እንዲሁም ያለ ባለስልጣኑ ፈቃድ ይፋ ማድረግ እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...