ያንጎ ኢትዮጵያ ከአሚጎስ ጋር በመተባበር የኢቪ ተሽከርካሪዎች የፋይናንስ ፕሮግራም ጀመረ

Date:

በኢትዮጵያ የያንጎ አገልግሎት ኦፕሬተር በሆነው በ’’G2G IT Solutions S.C’’ አማካኝነት በኢትዮጵያ ተኣማኒነት ካለው ከአሚጎስ SACCO የኢትዮጵያ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ጋር የመግባቢያ ስምምነት (MOU) መፈራረሙን ሲያሳውቅ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል። ይህ አጋርነት በያንጎ ኬርስ ስር ለኤሌክትሮኒክ መኪና ተሽከርካሪዎች አስተማማኝ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ ለማድረግ እና አሽከርካሪዎች የመኪና ባለቤት እንዲሆኑ ለማበረታታት ያለመ ተነሳሽነት ነው።

በመርሃ ግብሩ እስከ 100 የሚደርሱ የያንጎ አጋር አሽከርካሪዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በ17 ወራት ውስጥ እንዲገዙ ለማድረግ ከአሚጎስ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት የስራ አፈፃፀም መስፈርቶችን የሚያሟሉ ስድስት ብቁ ተሽከርካሪዎች በየወሩ ለተሽከርካሪዎች ግዢነት ይመደባሉ። አብዛኞቹ አጋር አሽከርካሪዎች በአሁኑ ጊዜ በኪራይ ተሽከርካሪዎች የሚንቀሳቀሱ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህም ገቢያቸው እና ነፃነታቸው እንዲገደብ አድርጓል፣ በመሆኑም ይህ ስትራቴጂያዊ ጥረት በኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው አሽከርካሪዎች ለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች ቀጥተኛ ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል።

የያንጎ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ይቅናአለም አበበ እንዳሉት “ይህ መርሃ ግብር ያንጎ ለውጥ ላይ እንደሚያተኩር የሚያሳይ ነው። ከኛ ጋር በአጋርነት የሰራ እያንዳንዱ አጋር አሽከርካሪ ነገ የማደግ እድል እንደሚያገኝ እናምናለን። ሆኖም ከኛ ጋር አጋር በመሆን ከተማችን ውስጥ በአሽከርካሪነት ለሚሰሩ ሰዎች አዳዲስ ኢኮኖሚያዊ እድሎችን እየፈጠርን እንገኛለን።”

የያንጎ ኦፕሬተር ኩባንያ የሆነው የG2G ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር አቶ ቴድሮስ መሃሪ በበኩላቸው “በዚህ ተነሳሽነት ያንጎ የጉዞ አገልግሎት አሰጣጥ እንቅፋቶችን ከመቀነሱ በተጨማሪ ለአሽከርካሪዎች የረጅም ጊዜ ጥቅሞችን የሚሰጥ የበለጠ ሁሉን አቀፍ ሥነ-ምህዳር በመገንባት ላይ ይገኛል። በመርሃ ግብሩ ውስጥ የተመዘገቡ አጋር አሽከርካሪዎች የገንዘብ ድጋፍን ብቻ ሳይሆን የፋይናንስ ትምህርት ድጋፍን ፣ የተሸከርካሪ ጥገና ምክሮችን እና ተለዋዋጭ የመክፈያ ዕቅዶችን በተጨማሪነት ያገኛሉ’’ ሲሉ ተናግረዋል።

“አሚጎስ ኃላፊነት የሚሰማው እና የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማጎልበት ቁርጠኛ አላማ ያለው ተቋም ነው” ሲሉ የተናገሩት የአሚጎስ ሥራ አስፈፃሚ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ርእሶም አክለውም “ከያንጎ ጋር በመተባበር በአሽከርካሪዎች ፋይናንስ ላይ ያለውን ወሳኝ ክፍተት እየፈታን እና በትብብር ሴክተሩ ጤናማ የኢኮኖሚ ጉልበት እንዲፈጥር ድጋፋችንን ማሳየታችንን እንቀጥላለን” ሲሉ ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ ተሳታፊ አጋር አሽከርካሪዎች በባህላዊ ነዳጅ ከሚንቀሳቀሱ መኪኖች ወደ አዲስ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች (ኢቪ) የሚሸጋገሩ ሲሆን ይህም ጥራቱን የጠበቀ፣ የበለጠ ዘላቂ እና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆነ አማራጭን ይሰጣል። በዚህም አጋር አሽከርካሪዎች የባለቤትነት መብት ሲያገኙ፣ ተሳፋሪዎች ከአስተማማኝ እና ምቹ የጉዞ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን በማረጋገጥ ከተማዋ ልህቀት ያለው ልምምድን ለማዳበር የምታደርገውን ጉዞ ያሳልጣል።

ባሳለፍነው አመት በኢትዮጵያ የተጀመረው የያንጎ ኬርስ ፕሮግራም ባለ ብዙ ዘርፍ ጅምር ሲሆን የአጋር አሽከርካሪዎችን ደህንነት እና የፋይናንስ መረጋጋት ማሻሻል ላይ ያተኮረ መሆኑ የሚታወስ ነው። በያንጎ ኬርስ ስር በተደረጉት ቀደምት ስራዎች፣ ኩባንያው የጤንነት ምርመራን፣ የአሽከርካሪዎች ትምህርት ፕሮግራሞችን እና ከፍተኛ የስራ አፈጻጸም ላላቸው አጋር አሽከርካሪዎች እውቅና ሰጥቷል።

ይህ የፋይናንስ አጋርነት በያንጎ ኬርስ የለውጥ ሂደት ውስጥ ታላቅ የሆነ ቀጣይ እርምጃን የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህም የያንጎን ዓላማ እና ለፈጠራ ያለውን ቁርጠኝነት ያጠናክራል።
በዚህ ተነሳሽነት ለመሳተፍ የሚፈልጉ አጋር አሽከርካሪዎች የያንጎ ቴሌግራም ግሩፕን በ ‘’https://t.me/ShuuFareMembersDiscussion’’
ላይ እንዲቀላቀሉ እናበረታታለን። አልያም የያንጎ አሽከርካሪዎች ድጋፍ ማዕከልን በጌቱ ንግድ ማዕከል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ይጎብኙ። የማመልከቻ እና የምዝገባ ሂደቱ ክፍት ሲሆን በያንጎ ቡድን አባላት አማካኝነት በቦታው ላይ በመገኘት የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንዲወስዱ ተጋብዘዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...