የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ዛሬ ደጋፊው በነቂስ ወጥቶ እንዲያበረታታቸው ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከዩጋንዳ ጋር ወሳኝ ጨዋታውን ያደርጋል።
ከጨዋታው በፊት አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ዚመር “ ደጋፊው በነቂስ ወጥቶ እንደሚደግፈን ተስፋ አደርጋለሁ “ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ቡድኑ ጥሩ ዝግጅት ማድረጉን ያነሱት አሰልጣኙ ለዩጋንዳ ክብር እንደሚሰጡ ገልፀው እነሱ በእግርኳሱ ጥሩ እየሰሩ ያሉ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።
“ ቡድኑ ተረጋግቶ እንዲፎካከር ሰርተናል “ ያሉት አሰልጣኙ “ የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ ለሀገራቸው በፍቅር እንዲጫወቱ አሳስበናል ብለዋል።
የቡድኑ አምበል ቢኒያም አብረሀ በበኩሉ “ ከዚህ በፊት እንዳደረጋችሁት ዛሬም ድጋፋችሁን ስጡን እንጠብቃችኋለን “ ሲል ለደጋፊው መልዕክቱን አስተላልፏል።
@tikvahethsport
