ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) እና ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በስምምነቱ መሠረትም ባንኩ በትራንስፖርትና የተለያዩ የንግድ ዘርፎች ተሰማርቶ ለሚገኘው ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ድርጅት ወይም ያንጎ ባይ ኤሌጋንስ ለሜትር ታክሲ ትራንስፓርት አገልግሎት ለሚያውላቸው የመጀመሪያ ዙር እስከ 50 የሚደርሱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ ከወለድ ነጻ በሆነ መንገድ ፋይናንስ ለማቅረብ ስምምነት አድርገዋል፡፡
ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ድርጅት በስሩ ካሉት ድርጅቶች ዉስጥ አንዱ በሆነዉ ያንጎ ባይ ኤሌጋንስ የትራንስፓርት አገልግሎት ሰጪ ተቋም ሲሆን በሀገሪቱ የትራንሰፖርት ዘርፍ ውጤታማ የሆነ ሀገር በቀል ተቋም ነው::
