ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢንቨስትመንቶቹን ከሲሚንቶና ማዳበሪያ ባሻገር በሌሎች ዘርፎችም ለማስፋፋት በዝግጅት ላይ ሲሆን፤ ወደ ወርቅ ማውጣትና የሪል እስቴት ዘርፉ ለመግባት ማቀዱ ተሰምቷል፡፡
የዳንጎቴ ግሩፕ ሊቀመንበር አሊኮ ዳንጎቴ፣ ከሰሞኑ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የማዳበሪያ ማምረቻ ፕሮጀክት ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ “የወርቅ ማዕድን ዘርፍ ላይ የመሰማራት እድሎችን እየተመለከትን ነው፣ እነዚህ ለኛ አዳዲስ ስራዎች ናቸው፣ ነገር ግን እንደ ስራ ፈጣሪ ኩባንያ እያንዳንዱን ኢንቬስትመንት እንፈልጋለን። ወደ ሪል እስቴትና አፓርታማ ግንባታዎችም ልንገባ እንችላለን” ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ውስጥ ጠንካራ መሰረት ያለው ዳንጎቴ ግሩፕ፤ አሁን ደግሞ ወደ ሪል እስቴትና ወርቅ ማውጣት ዘርፍ ለመግባት ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡
